የትግራይ ወቅታዊ ሁኔታ በ ዱረቲ መልኣኩ

Ethiopia related news and publications
Post Reply
africangear
Posts: 404
Joined: Fri Dec 11, 2020 5:07 pm

የትግራይ ወቅታዊ ሁኔታ በ ዱረቲ መልኣኩ

Post by africangear »

Almeda-Destruction.jpg
ከ 27 ቀናት በኋላ ፊንፊኔ ገብተናል።

ነገሮች የተስተካከሉ መስሎን ከምሰራበት NGO የስራ ባልደረቦች ጋር ሆነን በቀን አንዴ ወደ መቀሌ በረራ የሚደረገውን ተራ ጠብቀን ወደ ትግራይ ለስራ ጉዳይ አቀናን።
በአንፃራዊነት ሰላም የነበረችው ትግራይ በለቅሶ እና በዋይታ ተሞልታለች። ነገሮች ሚዲያ ላይ እንደሚነገሩት ሳይሆን ከባድ ነው።

የትግራይ ከተሞች ከአላማጣ እስከ አዲግራት ማብራት ተመልሶላቸዋል። ከአዲግራት በኋላ ግን ማብራት የሚባል የለም የዚህም ምክንያት የማባራት ኃይል ሰዎች ጦርነት እየተደረገ በመሆኑ በጦርነት መኃል እንጎዳለን በማለታቸው ነው።

የትግራይ ከተሞች የከተማ ፖሊስ የለም ። አስተዳደራዊ መዋቅሮች ፈርሷል። ዘርፊያ ተጧጡፏል ። ወጣቱ ወደ በረሃ ገብቷል። የከተሞችን ፀጥታ ለማስጠበቅ ከአማራ እና ከደቡብ ክልል የተመለመሉ የ7 ቀን ስልጠና የወሰዱ ቢኖሩም በግንባር ላይ ያለው ጦርነት በመቀጠሉ በግዳጅ ወደ ጦርነት ቦታው ተወስደዋል።

መደበኛ የመንግስት ስራ ይጀመር ቢባልም እስካሁን ስራ አልተጀመረም ። መስራያቤቶች ተዘርፏል። ከኮምፒየተር እስከጠረፔዛ ዘርፊያ ተፈፅሟል። ለዚህም ዘርፊያ የኤርትራ ወታደሮች የጠቀሳሉ። ከመቀሌ እና ከሺሬ ውጪ የኤርትራ ወታደሮች የሌሉበት የለም።

በግንባር ላይ ባለው ጦርነት ብዙ ወታደር በማለቁም የኤርትራ ወታደሮችን በመጠቀም የከተማው ኗዋሪ ላይ ሽብር እየተደረገበት ነው። እንደ ማስፈራሪያም የኤርትራ ወታደርን እንጠራባችኋለን ይባላል። በአዲግራት የኤርትራ ወታደሮች የኤርትራን መታወቂያ በማዘጋጀት በኤርትራ ስር ነው የምትዳደሩት በማለት ኗዋሪውን እያስጨነቁ ነው።

የኤርትራ ወታደሮች ዘረፋ ለመናገር ይከብዳል። በአድዋ ሆስፒታል በሽተኛችን ከተኛበት አልጋ በማስወረድ አልጋ እና ዊል ቸር ተዘርፏል። የህክምና ቁሳቁስ በመዘረፉም ሰዎች ከህክምና እጦት የተነሳ ህይወታቸውን እያጡ ነው። አርዓያ አሽከርካሪ የነበር ትርፍ አንጀት ይዞት ሆስፒታል ቢወስድም የቅዶ ህክምና ማድረጊያ ምላጭ እና መስፊያ በሙሉ በመዘረፉ ህክምና ሳያገኝ ህይወቱ አልፏል። ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ በስተቀር አዲግራት እና በአክሱም ዩኒቨርሲቲ ተዘርፎ ባዶውን ቀርቷል። ኮምፒየትር ጠርጴዛ ተሽከርካሪ መኪኖች በሙሉ ተዘርፈዋል።

ገንዘብ የመቀየሩ ሂደት ሙሉ በሙሉ ባለመፈፀሙ የኤርትራ ወታደሮች አሮጌው ብር በብዛት በእጃቸው ስላለ 2 ሺህ አሮጌውን ብር በ1 ሺህ አዲሱ ብር ነዋሪውን አስገድደው ቀይረው ይወስዳሉ። ማንም ከልካይ የላቸውም።

መቀሌ ከውቅሮ አካባቢ በሚደረግ ጦርነት የከባድ መሳሪያን ድምፅ ከመስማት ውጪ ከሌሎቹ ከተሞች በአንፃራዊነት ጦርነት አይታይባትም። የከተማ ውስጥ የመንግስት መ/ቤት ግልጋሎት እምብዛም የለም። የከተማ ፖሊስ ባለመኖሩ ዝርፊያ ተጣጡፏል። በአስችኳይ ጊዜ አዋጁ የተነሳ ከ12:00 በኋላ እንቅሳቃሴ የለም። በእንድ ሰሞን እስከ አንድ ሰዓት እንቅሳቃሴ ተፈቅዷል በሚል ህዝቡ እንቅሳቃሴ ቢያደርግም የተሰማራው ወታደር ሰውን መግደል በመጀመሩ እንቅስቃፍሴ ሁሉ ተገቷል።

በአጠቃላይ በትግራይ እየተደረገ ያለው ጦርነት ያላለቅ ገናም የተጀመረ ሆኜ አግንቼዋለው። ነገሮች በሚዲያ እንደሚነገሩት ሳይሆን በጣም ዘግናኝ ነገሮች ነው ያሉት። በየ መንገዱ ታንኮች መኪኖች ተቃጥለዋል። የሰው ልጅ እንደ ቅጠል ረግፏል። የኤርትራ ወታደሮች የሞተባቸውን እያነሱ በመኪና ጭነው ይሄዳሉ።

ብልፅግና ከትግራይ ከተሞች ውጪ ገጥሩን አልያዘም። ጦርነቱ በቀላሉ የሚቆምም አይመስለኝም። የትግራይ ወጣቶች ቁጭት ከፊታቸው ይነበባል። ለነፍ*ኛ አንበረከክም ይላሉ። ወደ በረሃ የሚተመው ወጣት ቁጥር የለውም።

Source: https://www.facebook.com/dureti.melaku. ... 1185062195


Post Reply