Page 1 of 1

በአላማጣ ከተማ ከትናንት ምሽት ጀምሮ እስካሁን ሰዓት ድረስ የቀጠለ ዝርፊያ በአማራ የፀጥታ ሃይሎች እና ፋኖ በተባለው ቡድን እየተፈፀመ ይገኛል

Posted: Fri Jul 02, 2021 10:03 am
by africangear
alamata-city-tigray.jpg
በአላማጣ ከተማ ከትናንት ምሽት ጀምሮ እስካሁን ሰዓት ድረስ የቀጠለ ዝርፊያ በአማራ የፀጥታ ሃይሎች እና ፋኖ በተባለው ቡድን እየተፈፀመ ይገኛል። ዘራፊዎቹ ተደራጅተው ከነመኪኖቻቸው ከቆቦ ከተማ በኩል የመጡ መሆኑ ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

ከመንግሥት መስሪያ ቤቶች እስከ የግለሰብ መኖሪያ እና የንግድ ቦታዎች፣ በገበያ ማዕከል በመግባት ከወርቅ ቤቶች ጀምሮ እስከ ኤሌክትኖኒክስ እቃዎች እና ቡቲኮች፣ በከተማዋ አለ የተባለ ነገር ሁሉ በትላልቅ መኪኖች ተጭኖ ወደ ቆቦ እየተጓዘ ይገኛል።

ንብረታቸውን ለማስጣል በሚሞከሩ ግለሰቦች ላይም ዘራፊቹ እርምጃ እየወሰዱ ይገኛሉ። አንዳንድ ግለሰቦችም ከመኖሪያቸው ተወስደው የት እንደደረሱ አይታወቅም። ህዝቡ ጭንቅ ላይ መሆኑን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

ኣኽሱማይት ሚዲያ
25 ሰኔ 2013 ዓ/ም