በአንድ በረራ፣ ከስብሓት ጋር

Ethiopia related news and publications
Post Reply
africangear
Posts: 404
Joined: Fri Dec 11, 2020 5:07 pm

በአንድ በረራ፣ ከስብሓት ጋር

Post by africangear »

Sebhat-Nega.jpg
አቢይ አሕመድ ወደ ስልጣን እንደመጣ ክረምት አካባቢ ነው፣ አቦይ ሰብሃት በዳይሬክተርነት የሚመራው የውጭ ግነኙነት ሰትራተጅካዊ ጥናት ተቋም ከኔዘርላንዱ ክሊንትደን ጋር በጋራ ያዘጁት አንድ ፕሮግራም ነበር። የአውሮፖ ፅምረታዊ ሂደት (integration) በሚመለከት የሚሰጥ ሰሚናርና ስልጠና የፕሮግራሙ አካል ነው። ለምሰራቅ አፍሪካ ልምድ እንዲቀሰምበት ታስቦ የተዘጋጀ ነበር። የክረምቱ ጉዞ ክሊንተደን ወዳለበት ወደ ሄግ ነበር። እኔ ተቋሙ የሚያሳትመው የዲስኮርስ ጆርናል ኤድተርነቴ የሚጓዘው ቡድን አባል ነኝ። አቦይ ስብሃትም ከኛ ጋር ተጓዥ መሆኑን አውቂያለሁ። አውሮፕላን ውስጥ ገብተን ተቀምጠናል። ሙሉ ተሳፋሪ ስለነበረ ተፋፍገናል። እሰክንሳፈር የነበረው የፍትሻዎችና የትኬት እንግልት አድክሞኝ ነበር። በዛ ላይ፣ ሁሌም የመታሰር ያህል ሰሜት የሚፈጥርብኝ የመሃል ወንበር ነው የደረሰኝ። ሰው ደግሞ ገና እየገባ፣ እቃ ይሰቅላል፣ ያሰተካክላል፣ የኢኮኖሚ ክፍል ግርግር ማየት ራሱ ልብ ያደክማል።

የቢዝነስ ክፍል ተሳፍሬ አላውቅም። እዛ ቤት ያለውን ምቾት እያሰላሁ ግን ልየነታችንን አስባለሁ፣ ሃብታም ወይም ትልቅ ባለስልጣን መሆን የሚያሰገኘው አንዱ ጥቅም በሚል ልተወው ስል ኣቦይ ሰብሓት ትዝ አለኝ። እንደ VIP እንዴት በምቾት፣ በቢሰነስ ክፍል ዘና ብሎ እንደተቀመጠ በምናቤ ጎበኘሁት። እኔንም ቅናት ቢጤ ጎበኘኝ። ወዲያው ግን የ84 አመት ኣዛውንትነቱን አስታውሼ ሃፍረት ተሰማኝ። ትንሽ ቆይቶ አንድ ሹራብ የለበሰና ሻርፕ ኣንገቱ ላይ ጣል ያደረገ ሰው እኔ የተቀመጥኩበትን 27ኛውን ረድፍ አልፎ ወደ 30ኛው ረድፍ ሄደ፣ በኔ ወንበር ትዩዩ ሲቀመጥም አየሁት። ሰብሓት ነበር። ማመን አቃተኝ። ይኸን በኢስታንቡል በኩል አውሮፕላን እያቀጣጠልን የምንጓዘው ዘወርዋራና የሩቅ በረራ እንዴት ሊቋቋመው ነው፣ ብየ ተገረምኩ። በኋላ እንዳየሁት ግን አጉል ሃዜኔታ ነው፣ እንደውም ከኣንዳንዶቻችን የተሻለ ጥንካሬ ነበረው።

ዘ-ሄይግ እንደደረሰን፣ የተገኝንለት ያህል ሆቴሉ ሎቢ ውስጥ ሰበሰበንና ስልጠናውን (እሱ ስልጠና እያለ ነበር የሚጠራው) ችላ እንዳንለው በአደራ መልክ አሳሰበን። "አውሮፓ ለህዝቦቻቸው ያመጡለት ትልቁ ፀጋ ልማትና ዲሞክራሲ እንዳይመስላቹህ፣ ጦርነት የሚባል ነገር እሰከዘላለሙ ማሰቀረታቸው ነው" አለን። ጦርነቱ የቀረላቸው መጀመሪያ ለጦርነት ከፍተኛ ግብኣት የነበራቸው coal and steel የተባሉት ስትራተጂክ ምርቶቾን በጋራ ለመቆጣጠር ብለው የጀመሩት ትስስር ወደ ጋራ ገበያና ኢኮኖሚ ሁሉን አቀፍ ትስስር ማደጉ የህብረቱ ትልቁ ስኬት መሆኑ ነገረን። ለዚህ ሲባል ብዙህነታቸውን በመቻቻልና በህግ ማስታመም እንደቻሉም ኣብራርልን።

አቦይ ሰብሓት ቀጠናችን የጦርነት ትኩሳትና ድባብ የማይለየው እንደመሆኑ ከአውሮፓው ስኬታማ የውህደት ትስስር ብዙ ጠቃሚ ልምድ መውሰድ እንደምንችል እንደ አገራዊ ተልእኮ እንደናስበው አስገነዘበን። ቀጥሎ የነገረን ሃሳብ ግን የትም ቦታ ሰምቼው ኣላውቅም። "በምስራቅ አፍሪካ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ትስስር ቢፈጠር ማህበራዊና የባህል ትስስሩን ያግዛል። በኛ ሁኔታ የውህደት ትስስሩ ወይም ኢንተግሬሽኑ ቢፈጠር በዚያ ምክንያት የሚፈጠር ብዘሃነት ሳይሆን የሚቀነስ ብዘሃነት ነው የሚኖረው" አለ። "የሚቀነስ ብዝሃነት" ምን ማለት እንደሆነ እንዲያብርራራ ጠየቅነው። ሲያብራራም፣ "ለምሳሌ ሶስት ኣፋሮች፣ ሁለት ኩናማዎች፣ ሁለት ኦሮሞዎች፣ ሁለት ተግሬዎች፣ 5 ወይም ከዚያ በላይ ሶማሌዎች... ወዘተ ቀርተው ኣንድ፣ ኣንድ፣አንድ፣… ይሆናሉ ማለት ነው።"

ይህ አንግዲህ እንደደደርስን፣ ስልጠናው ሳይጀመር በዋዜማው በንቃት እንድንከታተልና እንድንሳተፍ ለማሳሰብ ኣስቦ ሲነግረን የመከረን ነው። የአንድ ሳምንት ስልጠናውን በቁም ነገር ተከታትለናል። እሱም ራሱ ንቁ ተሳታፊ ነበር። ብዙ ጠቃሚ ነገርም አግኝተናል። እኔ ግን ከስልጠናው በላይ ኣቦይ ስብሓት ያለን ነገር ነው ጎልቶ የሚታወሰኝ። አካባቢያችን የተለያየው በፖለቲካና በኢኮኖሚ ነው። ይህም ልዩነት ከባህልና ማንነታዊ ትስስሩ ጋር ከፍተኛ ግጭት እየፈጠረ የጦርነት ሁኔታ እንዳይለየን አድርጓል። ስብሓት ኢኮኖሚውና ፖለቲካው ከተፈጥሯዊ ትሥሩ ጋር ስለማስታረቅ ነበር የነገረን።

አሁን ስብሓትን ሳስብ የበረሃው አንበሳ በሚል የሚታወቀው የሊቢያው አርበኛ ዑመር ሙኽታር ነው የሚታወሰኝ። እርግጥ ነው የሊቢያው ዑመር ስልጣንን ከህዝብ ልብ እንጂ ከህዝብ ድምፅ አላገኛትም። ሰብሓት ግን ድርጅት መርቶ፣ ህዝብ አሰተባብሮ ደርግን አሸንፎ፣ ስልጣን ላይ የደረሰና ሺዎች ተኪዎች ያፈራ አርበኛ ነው። የአርበኝነት ትእምርተነቱ ካልሆነ በቀር አሁን በኃላፊነትም በወንጀልም የለበትም። ከዚህ ቅሌት ብዙ አብሮነትን የሚጠየፍ፣ ቅያሜን ያረገዘ ወጣት ይፈራል። አንድ ሰው እንደፃፈው፣ ከኢትዮጵያውነት አልፎ ምስራቅ አፍሪካን የማስተሳሰር ራእይ የሚያቀነቅነው ስብሓት ሙሉ እድሜውን የሚማር፣ ስለህዝብ እንጂ ስለራሱ ደንታ የሌለው፣ ልበ ሙሉ ተራማጅ ታጋይ እንደሆነ የሚያወቁ ጥቂቶች ናቸው።

Source: https://www.facebook.com/dade.desta.1?_ ... =-UC%2CP-R


Post Reply